am_luk_text_ulb/09/12.txt

1 line
863 B
Plaintext

\v 12 \v 13 \v 14 12 ቀኑ ወደ ምሽት ተቃረበ፣ አሥራ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡና “ያለንበት ቦታ ምንም የሌለበት ምድረ በዳ በመሆኑ ሕዝቡ በአካብቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማረፊያ ምግብ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት። 13 እርሱ ግን “የሚበሉትን ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፦ “ወጣ ብለን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በስተቀር አሁን ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የበለጠ አይደለም” አሉት። 14 በዚያ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበር። እርሱም ለደቀ መዛሙርቱ “ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በቡድን እንዲቀመጡ አድርጓቸው” አላቸው።