am_luk_text_ulb/08/24.txt

1 line
625 B
Plaintext

\v 24 በዚያን ጊዜ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው ‘ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ! መሞታችን ነው’ እያሉ ከእንቅልፉ ቀሰቀሱት። እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ማዕበል ገሰፀና ፀጥ አደረጋቸው። \v 25 ከዚህ በኋላም “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። ፍርሃት ይዟቸውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው “ነፋሳትንና ባሕርን የሚያዝ አንርሱም የሚታዘዙለት ይሄ ማን ነው? ተባባሉ።