am_luk_text_ulb/08/16.txt

1 line
709 B
Plaintext

\v 16 እንግዲህ አንድ ሰው መብራትን ካበራ በኋላ ጋን ውስጥ ወይም ከአልጋው ስር አያደርገውም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ሰው ብርሃኑን ማየት ይችል ዘንድ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል። \v 17 ይህም መሆን ያለበት የሚታወቅ እንጂ የሚደበቅ ታውቆ ወደ ብርሃን የሚወጣ እንጂ ምስጢር የሚሆን ነገር ስለሌለ ነው። \v 18 ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል ከሌለው ደግሞ እንዳለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።