am_luk_text_ulb/07/11.txt

1 line
883 B
Plaintext

\v 11 \v 12 \v 13 \v 14 \v 15 11-15 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ወደ ናይን ከተማ ሄድ፤ ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ አብረው ነበር። ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሞት አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር። ኢየሱስም ተመልክቷት እጅግ አዘነላትና “አታልቅሺ” ካላት በኋላ ወደ ቃሬዛው ጠጋ ብሎ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፣ “አንተ ጎበዝ ተነሣ” አለው። ጎበዙም ተነሥቶ ተነጋገረ፤ ኢየሱስም ልጁን ለእናትዬው ሰጣት።