am_luk_text_ulb/17/22.txt

1 line
608 B
Plaintext

\v 22 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤" ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትናፍቁበት ቀን ይመጣል። ነገር ግን አታዩትም። \v 23 ሰዎች፣ ' እነሆ፣ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!' ይሉአችኋል። ነገር ግን እነርሱን ሰምታችሁ አትፈልጉ፤ አትከተሉአቸውም። \v 24 መብረቅ በሰማይ ላይ ሲበርቅ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።