am_luk_text_ulb/18/18.txt

1 line
721 B
Plaintext

\v 18 ከአለቆች አንዱ ኢየሱስን፣ "ቸር መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?" ብሎ ጠየቀው። \v 19 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "ለምን ቸር ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስቀር ቸር የለም። \v 20 ትእዛዛትን ሁሉ ታውቃቸዋለህ፤ እነርሱም፣ 'አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ እናትህንና አባትህን አክብር የሚሉ ናቸው።" \v 21 አለቃውም ፣ "እነዚህንማ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአቸዋለሁ።"