am_luk_text_ulb/18/03.txt

1 line
654 B
Plaintext

\v 3 አንዲት ባል የሞተባት ሴትም በዚያ ከተማ ነበረች። እርስዋም ዘወትር ወደ ዳኛው እየመጣች፣ 'ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍረድልኝ' ትለው ነበር። \v 4 ዳኛውም ለረጅም ጊዜ ሊረዳት ፈቃደኛ አልነበረም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ ብሎ አሰበ፤ \v 5 'ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ይህች ባል የሞተባት ሴት አዘውትራ በመምጣት እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ።' "