\v 13 ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡ \v 14 ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡