am_luk_text_ulb/14/07.txt

1 line
674 B
Plaintext

\v 7 ኢየሱስ በግብዣ ቦታ የከበሬታ ወንበር ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ በተመለከት ጊዜ እንዲህ በማለት አንድ ምሳሌ \v 8 ነገራቸው፤ "አንድ ሰው ወደ ሰርግ ግብዣ ቢጠራህ በመጀመሪያ በከበሬታ ቦታ አትቀመጥ፣ ምናልባት በዚያ ቦታ የሚቀመጥ ከአንተ ይልቅ ክብር የሚሰጠው ሰው ተጋብዞ ይሆናል፡፡ \v 9 ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው መጥቶ፣ 'ይህን ቦታ ለሌላ ሰው ልቀቅለት' ይልሃል፣ ከዚያም አንተ በሃፍረት ወደ ዝቅተኛ ቦታ ትሄዳለህ፡፡