am_luk_text_ulb/13/01.txt

1 line
698 B
Plaintext

\c 13 \v 1 በዚያን ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ የገሊላ ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ጲላጦስ ስለ ገደላቸውና ደማቸውንም ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀባቸው ሰዎች ነገሩት፡፡ \v 2 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "እነዚያ የገሊላ ሰዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው በዙሪያቸው ካሉት ከሌሎች የገሊላ ሰዎች ይልቅ ኅጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን? \v 3 አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ ።