am_luk_text_ulb/12/51.txt

1 line
610 B
Plaintext

\v 51 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት እንደ መጣሁ ታስባላችሁን? እንደዚያ አታስቡ፣ እነግራችኋለሁ፣ የመጣሁት ይልቁኑ መለያየትን ላመጣ ነው፡፡ \v 52 ከእንግዲህ ወዲህ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ሰዎች ቢኖሩ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፣ ሁለቱም በሦስቱ ላይ የሚነሡና የሚለያዩ ይሆናሉ፡፡ \v 53 አባት በልጅ ላይ ልጅም በአባት ላይ፤ አማት በምራት ላይ፣ ምራትም በአማት ላይ ይነሡና ይለያያሉ፡፡