am_luk_text_ulb/11/49.txt

1 line
709 B
Plaintext

\v 49 በዚህ ምክንያት በእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ተብሏል፣ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን ያሳድዳሉ ይገድሉማል። \v 50 ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው’። \v 51 ተጠያቂ የሚሆነውም ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ነው። አዎን፣ ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው እላችኋለሁ።