am_luk_text_ulb/11/33.txt

1 line
949 B
Plaintext

\v 33 አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ብርሃኑ በማይታይበት ሰዋራ ስፍራ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ በላዩ ላይ አይደፋበትም። ነገር ግን ወደዚያ ቤት የሚገቡ እንዲታያቸው ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል። \v 34 ዓይን የሰውነት መብራት ነው። ዓይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዓይንህ ሕመምተኛ ከሆነ ግን መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል። \v 35 ስለዚህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። \v 36 እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ የሌለበትና በብርሃን የተሞላ ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ በሙሉ ብርሃኑ መብራት በአንተ ላይ እንደሚያበራ ያህል ይሆናል።