am_luk_text_ulb/09/12.txt

1 line
890 B
Plaintext

\v 12 ቀኑ ወደ መገባደድ ተቃረበ፣ ዐሥራ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡና “ያለንበት ቦታ ምንም የሌለበት ምድረ በዳ በመሆኑ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማረፊያ ቦታና ምግብ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት። \v 13 እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “ወጣ ብለን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በስተቀር አሁን ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዐሣ የበለጠ አይደለም” አሉት። \v 14 በዚያ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በቡድን እንዲቀመጡ አድርጓቸው” አላቸው።