am_luk_text_ulb/08/51.txt

1 line
578 B
Plaintext

\v 51 ከዚያም እርሱ ወደዚያ ቤት በመጣ ጊዜ፣ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስ፣ ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና ከእናትዋ በስተቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም። \v 52 በዚያ ስፍራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ያለቅሱ ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ ልጅትዋ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አለ። \v 53 እነርሱ ግን መሞቷን ዐውቀው ስለ ነበር፣ በንቀት ሳቁበት።