am_luk_text_ulb/08/28.txt

1 line
755 B
Plaintext

\v 28 ኢየሱስን ባየው ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅም ድምፅ፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እኔ ከአንተ ምን ጉዳይ አለኝ?እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለው። \v 29 እንደዚህም ያለበት ምክንያት ብዙ ጊዜ ይይዘውና ያሠቃየው የነበረውን ርኩስ መንፈስ ከእርሱ እንዲወጣ ኢየሱስ አዞት ስለነበር ነው። ምንም እንኳ በብረት ሰንሰለት የታሰረና በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ቢሆንም፣ እስራቱን ይበጥስ፣ በአጋንንቱም ግፊት ወደ በረሐ እየሄደ ይንከራተት ነበር።