am_luk_text_ulb/07/36.txt

1 line
720 B
Plaintext

\v 36 አንድ ፈሪሳዊም በቤቱ ዐብሮት እንዲመገብ ኢየሱስን ጋበዘው ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ማዕዱ ቀረበ። \v 37 እነሆ፣ በዚያ ከተማ በመጥፎ ምግባሯ የታወቀች እንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ተጋብዞ በማዕድ እንደ ተቀመጠ ተረድታ የአልባስጥሮስ ሽቱ ብልቃጥ ይዛ ወደ ቤቱ ገባችና \v 38 ከኢየሱስ በስተኋላ ከእግሩ አጠገብ ቆማ ማልቀስ ጀመረች። ከዚያም በእንባዋ እግሩን ማራስና በፀጉሯም ማበስ ቀጠለች፣ እግሩንም ትስመው በሽቱም ትቀባው ነበር።