am_luk_text_ulb/07/24.txt

1 line
728 B
Plaintext

\v 24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመር፣ “ምን ልታዩ ወደ በረሐ ወጣችሁ በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን? \v 25 ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነውን? እነሆ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በአብያተ መንግሥታት ነው። \v 26 ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይን ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይን ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው።