am_luk_text_ulb/07/11.txt

1 line
957 B
Plaintext

\v 11 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ናይን ወደ ምትባል ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ዐብረውት ይሄዱ ነበር። \v 12 ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሰው ሞቶ አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር። \v 13 ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት። \v 14 ከዚያም ወደ ቃሬዛው ተጠግቶ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። ኢየሱስ፣ “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ” አለ። \v 15 ወጣቱም ተነሥቶ መናገር ጀመረ፤ ከዚያም ኢየሱስ ልጁን ለእናትዮዋ ሰጣት።