\v 12 በዚያም ወቅት ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፣ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡ \v 13 በነጋም ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራ፣ ከእነርሱም ‘ሐዋርያት’ ብሎ የሰየማቸውን አሥራ ሁለቱን መረጠ፡፡