am_luk_text_ulb/05/29.txt

1 line
937 B
Plaintext

\v 29 ከዚያ በኋላ፣ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፣ በዚያም ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና በማዕድ ቀርበው ከእነርሱ ጋር የሚመገቡ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡ \v 30 ነገር ግን ፈሪሳውያንና ጻሐፍት በደቀመዛሙርቱ ላይ፣ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ለምን ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም?” እያሉ ያጉረመርሙባቸው ነበር፡፡ \v 31 ኢየሱስም እንደዚህ በማለት መለሰላቸው፣ “በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሐኪም አያስፈልጋቸውም፣ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ብቻ ናቸው፡፡ \v 32 እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ለንስሐ ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፡፡”