am_luk_text_ulb/05/22.txt

1 line
561 B
Plaintext

\v 22 ነገር ግን ኢየሱስ ምን እንዳሰቡ አውቆ፣ “በልባችሁ ይህንን ለምን ትጠይቃላችሁ? \v 23 የትኛውን ማለት ይቀላል፡- ‘ኃጢአትህ ተሰረየችልህ’ ማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ማለት? \v 24 ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣ ለአንተ፣ ‘ተነሣና ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ’ ብዬ እናገራለሁ፡፡"