am_luk_text_ulb/05/04.txt

1 line
817 B
Plaintext

\v 4 ንግግሩንም በጨረሰ ጊዜ ለስምዖን፣ “ጀልባይቱን ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ አድርጋትና ዓሣ ለማጥመድ መረቦቻችሁን ጣሉ፡፡” አለው፡፡ \v 5 ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፣ ሌሊቱን ሁሉ ስንሠራ አደርን ምንም አላጠመድንም፣ ነገር ግን በቃልህ መረቡን እጥላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡ \v 6 ይህንን ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፣ መረቦቻቸውም ሊቀደዱ ደረሱ፡፡ \v 7 ስለዚህ እንዲመጡና እንዲረዷቸው በሌላ ጀልባ የነበሩትን ጓደኞቻቸውን በጥቅሻ ጠሩ፡፡ እነርሱም መጥተው ሁለቱንም ጀልባዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው፡፡