|
\v 5 ከዚያ በኋላም ዲያብሎስ ከፍ ወዳለ ስፍራ ወሰደውና፣ በቅጽበት የዓለም መንግሥታትን ሁሉ አሳየው፡፡ \v 6 ዲያብሎስም ለእርሱ፣ “እነዚህን ሁሉ መንግሥታት ከክብራቸው ሁሉ ጋር እንድትገዛ እኔ ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ ይህንን ማድረግ የምችለው እገዛቸው ዘንድ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነው፣ እኔም ለምፈልገው ለማንኛውም ሰው ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡ \v 7 ስለዚህ በፊቴ ብትሰግድልኝና ብታመልከኝ፣ ይሄ ሁሉ የአንተ ይሆናል አለው። |