am_jud_text_ulb/01/12.txt

1 line
713 B
Plaintext

\v 12 እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ አብረዋችሁ ሲጋበዙ ችግር የሚፈጥሩባችሁ ድብቅ እንቅፋቶች ናቸው፤ ደግሞም ያለ ሃፍረት ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው። እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ውሃ አልባ ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው፥ ከሥራቸው የተነቀሉና ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው። \v 13 የራሳቸውን የነውር አረፋ የሚደፍቁ የተቆጣ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማም ለዘላለም የተጠበቀላቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።