am_jud_text_ulb/01/09.txt

1 line
756 B
Plaintext

\v 9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ዲያብሎስን በመቃወም ስለ ሙሴ ሥጋ በተከራከረው ጊዜ «ጌታ ይገሥጽህ» አለው እንጂ በእርሱ ላይ ሊፈርድ ወይም አንዳች የስድብ ቃል ሊናገር አልደፈረም። \v 10 እነዚህ ሰዎች ግን የማያውቋቸውን ነገሮች ሁሉ ይሳደባሉ። እነርሱም አእምሮ የሌላቸው እንስሳት እንደሚያደርጉት በደመ ነፍስ በሚያውቋቸው ነገሮች ይጠፋሉ። \v 11 ወዮላቸው፤ በቃየን መንገድ ሄደዋልና፤ለገንዘብ ሲሉ በበለዓም ስህተት ውስጥ ወድቀዋልና፤በቆሬም ዐመፅ ጠፍተዋልና።