am_jud_text_ulb/01/03.txt

1 line
757 B
Plaintext

\v 3 ወዳጆች ሆይ፤ አብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ ጥረት እያደረግሁ ሳለ፥ ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለተሰጠው እምነት ጸንታችሁ ትጋደሉ ዘንድ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። \v 4 ለፍርድ እንደሚዳረጉ ከብዙ ዘመን በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና። እነዚህ ሰዎች ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው፥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በሴሰኝነት የሚለውጡ፥ እርሱ ብቻ ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።