Mon Aug 14 2017 12:42:38 GMT+0300 (Jordan Daylight Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2017-08-14 12:42:39 +03:00
parent 46a3be6e2a
commit e44c03ca2d
9 changed files with 11 additions and 0 deletions

1
09/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ከገባኦን የመጡት ሰዎች፣ “የአንተ አገልጋዮች መሆን እንፈልጋለን፡፡ እኛ ወደዚህ የመጣነው ከሩቅ ስፍራ ነው፣ የመጣነውም የአምላካችሁን የያህዌን ዝና ሰምተን ነው፡፡ እርሱ በግብጽ ያደረገውን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ሰምተናል፡፡ 10ደግሞ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ በሚኖሩት በሁለቱ የአሞራውያን ነገስታት፤ ሄስቦንን በሚገዛው በሴዎን እና በአስታሮት በሚኖረው በባሳን ንጉስ በአግ ንጉስ ላይ ምን እንዳደረሰ ሰምተናል፡፡

1
09/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ስለዚህም መሪዎቻችንና የተቀረውም ህዝባችን እንዲህ አሉን፣ ‹ጥቂት ስንቅ ይዛችሁ ከእስራኤላውያን ጋር ለመነጋገር ሂዱ፡፡ እንዲህም በሏቸው፣ “እኛ የእናንተ አገልጋዮች መሆን እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህ ከእኛ ጋር የሰላም ስምምነት አድርጉ፡፡” 12“የያዝነውን ዳቦ ተመልከቱ፡፡ ወደዚህ ለመምጣት ከቤታችን በተነሳንበት ቀን ትኩስና ያላደረ ነበር፡፡ አሁን ግን ደረቅና የሻገተ ሆኗል፡፡ 13ወይን መያዣ አቁማዳዎቻችን ተመልከቱ፣ ከስፍራችን ከመነሳታችን በፊት ወይን ስንሞላባቸው አዲስ ነበሩ፣ አሁን ግን ተቀደዋል አርጅተዋልም፡፡ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችንም ከመንገዱ ርቀት የተነሳ አርጅተዋል፡፡”

1
09/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
የእስራኤል መሪዎችም ከእነርሱ ጋር ስምምነት ለማድረግ ከአረጀው ምግባቸው ጥቂት ተቀብለው አብረዋቸውም በሉ፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም ያህዌን ለመጠየቅ አላሰቡም፡፡ 15በዚህ መልክ፣ ኢያሱ ሰላም ለማድረግ ተስማማ፡፡ እስራኤላውያን ከገባኦን ከመጡ ሰዎች ጋር ስምምነት አደረጉ፣ እነዚህን ባዕዳን ላለመግደል ተስማሙ፡፡ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በዚህ ነገር መሀላ አደረጉ፡፡

1
09/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ሆኖም፣ ከሶስት ቀናት በኋላ ሰዎቹ በአቅራቢያቸው የሚኖሩ የገባኦን ሰዎች መሆናቸውን እስራኤላውያኑ አወቁ፡፡ 17ስለዚህም ከገባኦን የመጡት ሰዎች ወደሚኖሩበት ሄዱ፡፡ ሶስት ቀናት ብቻ እንደተጓዙ፣ ወደ ከተሞቻቸው ወደ ገባኦን፣ ከፊራ፣ ብኤሮት እና ቂርያትይዓሪም ደረሱ፡፡

2
09/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
እስራኤላውያን ከእነርሱ ጋር በሰላም ለመኖር ተማምለው ስለነበረ እኒዚህን ከተሞች አልወጉም፤ ያህዌ የገቡትን ቃል ኪዳን ሰምቶ ነበርና፡፡
የእስራኤል ሰዎች ሁሉ በመሪዎቻቸው ላይ ከዚህ ስምምነት የተነሳ ተቆጡ፡፡ 19መሪዎቹ ግን፣ “እኛ ከእነርሱ ጋር በሰላም ለመኖር ቃል ገብተናል፣ የእስራኤል አምላክ ያህዌም ያንን ለማድረግ ቃል ስንገባ ሰምቷል፡፡

2
09/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
ብንገድላቸው፣ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ይቆጣል፣ በመሀላ የገባልናቸውን ቃል ኪዳን ባለመጠበቃችን ይቀጣናል፡፡ ነገር ግን ማድረግ የምንችለው ይህንን ነው፡፡
21በህይወት እንዲኖሩ እንፈቅድላቸዋለን፣ ነገር ግን እነርሱ የእኛ አገልጋዮች ይሆናሉ፣ እንጨት ይለቅማሉ ለህዝቡም ሁሉ ውሃ ይቀዳሉ፡፡” የሆነውም መሪዎቹ እንዳቀዱት እንደዛው ነው፡፡

1
09/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ከዚያም ኢያሱ ከገባኦን የመጡት ሰዎች ሰብስቦ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፣ “ለምን ዋሻችሁን ቤታችሁ ለእኛ ቅርብ ነው፣ የምትኖሩት በቅርባችን ነው፣ ነገር ግን የመጣነው ከሩቅ አገር ነው ብላችሁ ነገራችሁን! 23አሁን ከእርግማን በታች ትኖራላችሁ፡፡ የእኛ ባሮች ትሆናላች፡፡ ለዘለዓለም የእኛ ባሮች ትሆናላችሁ፣ እንጨት ለመቁረጥና ለአምላካችን ቤት ውሃ ለመቅዳት ትገደደላችሁ፡፡

1
09/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ከገባኦን የመጡት ሰዎች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ለእናንተ የዋሸነው ትገድሉናላችሁ ብለን ፈርተን ስለነበረ ነው፡፡ አምላካችሁ ያህዌ፣ ለአገልጋዩ ለሙሴ የእናንተ ህዝብ በከነዓን የምንኖረውን ሁላችንንም ገድላችሁ ምድራችንን ለእናንተ እንደሚሰጥ ነግሮት እንደነበር ሰምተናል፡፡ 25ስለዚህ አሁን በእኛ ላይ የምታደርጉትን ትወስናላችሁ፡፡ መልካም እና ትክክል መስሎ የታያችሁን ሁሉ አድርጉብን፡፡”

1
09/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ስለዚህም ኢያሱ የገባኦንን ሰዎች ህይወት አተረፈ፤ የእስራኤል ሰራዊት እንዲጎዷቸው አልፈቀደም፡፡ 27በምትኩ፣ የእስራኤላውያን ባሮች እንዲሆኑ አስገደዳቸው፡፡ ለእስራኤል እንጨት ቆራጭና ውሃ ቀጂ ሆኑ፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ መስዋዕት የሚያስፈልገውን እንጨትና ውሃ ያመጡ ነበር፡፡ እናም የገባኦን ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስም ያንን ያደርጋሉ፡፡