am_jol_text_ulb/03/01.txt

2 lines
650 B
Plaintext

\c 3 \v 1 እነሆ፥በዚያ ወራትና በዚያ ጊዜ፥የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ፥ \v 2 አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፥ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። በአሕዛብ መካከል ከበተኑአቸው ከሕዝቤና ከርስቴ ከእስራኤል የተነሳ፥ ምድሬን ከመከፋፈላቸው የተነሳ፤ በዚያ እፈር
ድባቸዋለሁ። \v 3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን በሴተኛ አዳሪ ለወጡ፥ ሴት ልጅንም ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ጠጡም።