am_jol_text_ulb/02/21.txt

1 line
757 B
Plaintext

\v 21 እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ምድር ሆይ አትፍሪ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሴትም አድርጊ። \v 22 የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳ ማሰማሪያዎች ለምልመዋልና፥ ዛፎች ፍሬያቸውን አፍርተዋልና፥ የበለስ ዛፎችና ወይኖች ሙሉ ፍሬያቸውን ሰጥተዋልና፤አትፍሩ። \v 23 የበልግን ዝናብ እንደሚገባ ይሰጣአችኋልና፥እንደ ቀድሞ ዘመን የበልግ ዝናብንና የፀደይን ዝናብ ያካፋላችኋልና፤ የጽዮን ሰዎች ሆይ፥ደስ ይበላችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ሐሴት አድርጉ።