\v 15 በጽዮን መለከት ንፉ፥የተቀደሰ ጾም አውጁ፥ የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። \v 16 ሕዝቡን ሰብስቡ፥የተቀደሰ ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችን፥ልጆችን፥ የሚጠቡትንም ሕጻናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከእልፍኛቸው፥ሙሽራይቱም ከጫጉላ ቤታቸው ይውጡ።