am_jol_text_ulb/02/01.txt

1 line
673 B
Plaintext

\c 2 \v 1 በጽዮን መለከት ንፉ፥ በቅዱስ ተራራዬም ላይ የማስጠንቀቂያ ድምጽ አሰሙ! የእግዚአብሔር ቀን መጥቷልና፥በእርግጥም ቅርብ ነውና፤የም ድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በፍርሃት ይንቀጥቀጡ። \v 2 እርሱም የጨለማና የጭጋግ ቀን፥የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። ንጋት በተራሮች ላይ እንደሚዘረጋ፥ታላቅና ኃያል ሠራዊት እየመጣ ነው። እርሱን የመሰለ ሠራዊት ከቶ አልነበረም፥ከብዙ ትውልድ በኋላ እንኳን ዳግመኛ አይኖርም።