am_jol_text_udb/02/26.txt

2 lines
687 B
Plaintext

\v 26 እናንተም የእኔ ሕዝብ ሆዳችሁ እስኪሞላ ድረስ ትበላላችሁ፤ ከዚያ በኋላም ስላደረግሁላችሁ ድንቅ ነገሮች እኔን አምላካችሁን ታመሰግናላችሁ፤ ከእንግደዲህ ሌሎች ዳግመኛ እንዲያሳፍሯችሁ በፍጹም አላደርግም፡፡
\v 27 ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ምንጊዜም በመካከላችሁ እንዳለሁ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እደሆንሁና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ዳግመኛ ሌሎች እንዲያሳፍራችሁ በፍጹም አልፈቅድም፡