am_jol_text_udb/02/10.txt

2 lines
696 B
Plaintext

\v 10 መሬት እንድትንገዳገድ ሰማይም እንዲንቀጠቀጥ እንደሚያደርጉ ያህል ነው፡፡ በሰማዩ ላይ እጅግ ብዙ አንበጦች ስለሚኖሩ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ክዋክብትም አያንፀባርቁም፡፡
\v 11 ሊቈጠር የማይችለውን ይህንን የአንበጣ ሠራዊት እግዚአብሔር ይመራዋል፤ እነርሱም የእርሱን ትእዛዝ ያከብራሉ፤ ማንም በሕይወት ሊተርፍ የሚችል እስከማይመስል ድረስ ይህ አሁን በእኛ ላይ የሚፈርድበትና እኛን የሚቀጣበት ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡