am_jol_text_udb/02/01.txt

2 lines
760 B
Plaintext

\c 2 \v 1 በእግዚአብሔር የተቀደሰ ተራራ በኢየሩሳሌም ባለው የጽዮን ተራራ መለከትን ንፉ! እግዚአብሔር እኛን በተጨማሪ የሚቀጣበት ጊዜ ፈጥኖ ስለሚደርስ መፍራትና መንቀጥቀጥ እንዳለባቸው ለይሁዳ ሕዝብ ተናገር፡፡
\v 2 ያ ቀን እጅግ ጨለማና ጭጋጋማ ቀን ነው፤ ጥቁር ደመና ስለሚኖር እጅግ ጨለማ ነው፤ ግዙፍ የአንበጣ መንጋ ተራራውን ስለሸፈነው እንደ ጥቁር ደመና ይሆናል፤ እንደዚህ ያለ ነገር ከዚህ ቀደም በፍጹም አልሆነም፤ እንደዚህ ያለ ነገር በፍጹም ዳግመኛ አይሆንም፡፡