\c 3 \v 1 እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፡- ‹‹በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌምና በይሁዳ ካሉ ሌሎች ቦታዎች ጠላቶቻቸው የወሰዷቸውን ሕዝቦች መልሼ አመጣቸዋለሁ፡፡ \v 2 ከዚያ በኋላ በኢዮሳፍጥ ሸለቆ የሌሎችን አገሮች ሕዝቦች ሁሉ እሰበስባለሁ፤ በእነርሱ ላይ እፈርዳለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ ምክንያቱም ሕዝቤን እስራኤልን በታትነዋቸዋል፤ ወደ ሌሎች አገሮችም እንዲሄዱ አስገድደዋቸዋል፤ ምድሬንም እርስ በርሳቸው ተከፋፍለዋል፡፡ \v 3 ከሕዝቤ እያንዳንዱን ለማግኘት ዕጣ ተጣጣሉ፣ ከዚያ በኋላም ለጋለሞችና ለሚጠጡት ወይን ጠጅ የሚከፍሉትን ለማግኘት ከእስራኤላውያን ወንዶችና ሴች ልጆች አንዳንዶቹን ሸጡአቸው፡፡