\v 16 እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ካለው የጽዮን ተራራ ይጮኻል፤ ድምፁም እንደ ነጐድጓድ ይሆናል፣ ሰማይንና ምድርንም ያናውጣል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ይጠብቃል፣ ከበስተኋላው የእስራኤል ሕዝብ እንደሚከለሉበት ጠንካራ ቅጥር ይሆናል፡፡ \v 17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹‹በዚያን ጊዜ እናንተ የእስራኤል ሕዝቦች እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ ለራሴ በለየሁት በጽዮን እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌም ለእኔ እጅግ የተለየች ከተማ ትሆናለች ከባዕድ አገሮች የመጡ ወታደሮችም ዳግመኛ በፍጹም ድል አያደርጓትም፡፡