\v 4 እናንተ የጢሮስና የሲዶና ሰዎች፣ እናንተም የፍልስጥኤም ሰዎች፣ በእኔ ላይ ተቈጥታችኋል ነገር ግን የምትቈጡበት ምንም ምክንያት የላችሁም፤ በእኔ ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ የምትሞክሩ ከሆነ፣ እኔ ፈጥኜ እበቀላችኋለሁ፡፡ \v 5 ከቤተ መቅደሴ ብርና ወርቅን እንዲሁም ሌሎች የከበሩ ነገሮችን ወስዳችሁ በራሳችሁ ቤተ መቅደሶች ላይ አደረጋችኋቸው፡፡ \v 6 በኢየሩሳሌምና በሌሎች የይሁዳ አካባቢዎች ያሉትን ሕዝቦች ጐትታችሁ ወደ ሩቅ ስፍራ ወስዳችኋቸው ለግሪከ ነጋዴዎችም ሸጣችኋቸው፡፡