\v 24 እህላችሁን የምትወቁበት አውድማ በእህል የተሸፈነ ይሆናል፤ ዐዲስ የወይን ጭማቂንና የወይራ ዘይትን የምታጠራቅሙባቸው ጋኖችም ሞልተው ይፈሳሉ፡፡ \v 25 እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፡- ‹‹እንዲያጠቃችሁ የላክሁባችሁ ያ ግዙፍ ሠራዊት፣ ታላቁ የአንበጣ መንጋ የደመሰሰባችሁን ማንኛውንም ነገር መልሼ እሰጣችኋለሁ፡፡