\v 8 እርስ በርሳቸው ሳይጋፉ ወደፊት ይገሠግሣሉ፤ ሰዎች ጦርና አንካሴ ቢወረውሩባቸውም ያ እንዲቆሙ አያደርጋቸውም፡፡ \v 9 በከተማ ቅጥሮች ላይ ይርመሰመሳሉ ወደ ቤቶቻችንም ይገባሉ፤ ሌቦች እንደሚያደርጉት በመስኮቶቻችን በኩል ይገባሉ፡፡