\v 6 ሰዎች መምጣታቸውን ሲመለከቱ እጅግ ይገረጣሉ ይፈሩማል፡፡ \v 7 ወታደሮች እንደሚያደርጉት አንበጦቹ በግድግዳዎች ላይ ይዘላሉ፤ ረድፋቸውንም ጠብቀው ይጓዛሉ እንጂ በፍጹም ከመስመራቸው ዝንፍ አይሉም (አይወጡም)፡፡