\v 5 እናንተ የሰከራችሁ ንቁ! ዘለላው ሁሉ ስለጠፉ፣ ዐዲስ ወይን ጠጅም ስለማይኖር ነቅታችሁ በከፍተኛ ድምፅ አልቅሱ! \v 6 ግዙፍ የአንበጣ መንጋ ወደ አገራችን ገብቷል፤ ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ወታደሮች እንዳሉት ብርቱ ሠራዊት ናቸው፤ አንበጦቹ እንደ አንበሳ ጥርሶች የተሳሉ ጥርሶች አሏቸው! \v 7 ቅርንጫፎቹ ተራቁተው ነጭ እስኪሆኑ በመላጥና ቅርፊቱን ሁሉ በመብላት የወይን ተክሎቻችንና የበለስ ዛፎቻችንን ደምስሰዋል፡፡