\c 1 \v 1 እኔ የባቱኤል ልጅ ኢዮኤል ነኝ፤ እግዚአብሔር ለእኔ የሰጠኝ መልእት ይህ ነው፡፡ \v 2 እናንተ የእስራኤል መሪዎችና በዚች አገር የምትኖሩ ማንኛችሁም ሰዎች ይህንን መልእክት አድምጡ! እኛ ወይም አባቶቻችን በኖሩበት ዘመን እንዲህ ያለ ነገር ከቶ ሆኖ ዐያውቅም፡፡ \v 3 እናንተ ለልጆቻችሁ ንገሩ፣ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው እንዲነግሯቸው ንገሯቸው፤ የልጅ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው እንዲነግሩ ንገሯቸው፡፡