am_jhn_text_ulb/12/34.txt

1 line
784 B
Plaintext

\v 34 ሕዝቡ፣ «ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ 'የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ?' ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?» ብለው መለሱለት። \v 35 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «አሁን ለጥቂት ጊዜ ብርሃን በመካከላችሁ አለ፤ ጨለማ እንዳይውጣችሁ በዚህ ብርሃን ተመላለሱ። በጨለማ የሚመላለስም ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። \v 36 የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።» ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከእነርሱ ተለየ፤ ተሰወረባቸውም።