\v 25 ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነገር ግን በዚህ ዓለም እያለ ሕይወቱን የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት እንድትጠበቅ ያደርጋታል። \v 26 ማንም ሊያገለግለኝ የሚወድ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። ማንም ቢያገለግለኝ አብ ያከብረዋል።