am_jhn_text_ulb/08/42.txt

1 line
879 B
Plaintext

\v 42 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ ስለ መጣሁ፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ በራሴም ፈቃድ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እርሱ ላከኝ። \v 43 ቃሌን የማትረዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። \v 44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለማድረግ ትመኛላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያውም ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ እውነት በእርሱ ዘንድ ስለሌለም፣ በእውነት አይጸናም። ሐሰትንም ሲናገር ከራሱ አፍልቆ ይናገራል፤ ምክንያቱም እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት ነው።