am_jhn_text_ulb/08/39.txt

1 line
691 B
Plaintext

\v 39 እነርሱም መልሰው፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ፣ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር። \v 40 አሁን ግን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ለመግደል ትፈልጋላችሁ። አብርሃምኮ ይህን አላደረገም። \v 41 እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፣ “እኛ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አንድ አባት እግዚአብሔር አለን” አሉት።