\v 3 ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡ \v 4 አባት ሆይ፣ እንዳከናውነው የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ፡፡ \v 5 አሁን አባት ሆይ፣ ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር ከአንተ ጋር አክብረኝ፡፡