am_jhn_text_ulb/15/20.txt

1 line
619 B
Plaintext

\v 20 'አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም' በማለት የነገርኋችሁን ቃል ልብ በሉ፤ እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ፣ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። \v 21 የላከኝን እርሱን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል። \v 22 እኔ ባልመጣና ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የለም።