\v 16 እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ነገር ግን እኔ መረጥኋችሁ፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ ሾምኋችሁ። ይህም አብን በስሜ የምትለምኑትን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጣችሁ ነው። \v 17 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።